መስከረም 14/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከመስከረም 05-14/2016 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ግዮን ሆቴል የመጀመሪያ ዙር የሕይወት አድን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በሀገራችን ያለውን የሰለጠነ የሕይወት አድን ባለሙያ እጥረትን የሚቀርፍ ከመሆኑም ባሻገር ኅብረተሰቡ በዋና ገንዳ በነፃነት እንዲዝናና እንዲሁም ከጥንቃቄ እውቀት እና ክሂሎት እጥረት በገንዳ አካባቢ የሚጠፋ ክቡር የሰው ልጅ ሕይወትን ለመታደግ የጎላ ድርሻ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
በፌዴሬሽኑ የተሰጠው ይህ የ2ኛ ደረጃ የውሃ ዋና ሕይወት አድን ስልጠና ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን የስልጠናውም ሂደት ሰላሳ በመቶ በንድፈ ሐሳብ እና ሰባ በመቶ በተግባር የተደገፈ ነው፡፡
በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሁለቱም ጾታ የተውጣጡ 26 ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡