መስከረም 29/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከመስከረም 19-28/2016ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ግዮን ሆቴል ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰረት ደምሴ በመልዕክታቸው ፌዴሬሽኑ ከተቋቋመ ረጂም አመታት ቢያስቆጥርም እንደ አገር የሚጠበቅብንን ሰርተናል ብለን አናምንም ለዚህም የመሠረተ ልማትና የአሰልጣኞች እጥረት ተግዳሮቶች እንደሆኑ አንስተዋል።
አያይዘውም አንዱን ተግዳሮት ለመሻገር ይሄ ስልጠና አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ስልጠናው እንዲሰጥ አድርገናል ብለዋል።
በተጨማሪም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጣችሁ ሰልጣኞች ውሃ ዋና ስፖርት እንደ አንድ ኮርስ እንዲሰጥ እና ተተኪ ከማፍራት አንጻር ሀላፊነት አለባችሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
በስልጠናው ከተለያዩ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለቱም ጾታ የተውጣጡ 21 አሰልጣኞች የተሳተፋ ሲሆን 16ቱ ተመርቀው የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡